የስክሪን ምርኮኛ የሆኑት ልጆቻችን እና የሳይንቲስቶች አዲሱ ምክረ-ሀሳብ
ልጅዎ በቀን 60 ደቂቃ ይንቀሳቀሳል በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ሕፃናትና ታዳጊዎች ከቀድሞው ትውልድ በተለየ መልኩ በአካላዊ እንቅስቃሴ ደካማ እየሆኑ መምጣታቸውን ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።
ልጅዎ በቀን 60 ደቂቃ ይንቀሳቀሳል በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ሕፃናትና ታዳጊዎች ከቀድሞው ትውልድ በተለየ መልኩ በአካላዊ እንቅስቃሴ ደካማ እየሆኑ መምጣታቸውን ተመራማሪዎች አስታውቀዋል። ይህ ተቀማጭነት (Sedentary lifestyle) እና ስክሪን ፊት ብዙ ሰዓት ማሳለፍ፣ በየቀኑ እየጨመረ ከመጣው የሕፃናት ውፍረት (Obesity) ጋር በቀጥታ የተያያዘ ሆኗል።በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ከ10 ሕፃናት መካከል አንዱ (1 in 10) ከመጠን ያለፈ ውፍረት ሰለባ እየሆነ ይገኛል። ለአካላዊ እንቅስቃሴ ማነስ እንደ ዋና ምክንያት የተጠቀሱት የቪዲዮ ጌሞች መብዛት፣ የስራ ጫና (Stress)፣ የተዘጋጁ ምግቦች (Fast Food) መዘውተር እና ወላጆች ልጆቻቸውን በስፖርት ላይ እንዲሳተፉ የሚያደርጉት ጥረት መቀነስ ናቸው።
ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ልጆችን "አካላዊ እንቅስቃሴ አድርጉ" ብሎ መገፋፋት ሳይሆን፣ እንቅስቃሴውን የዕለት ተዕለት ህይወታቸው አካል የሚያደርጉበት ማራኪ መንገዶችን መፍጠር ያስፈልጋል። በዚህ የሳምንት መጨረሻ ወላጆች ሊተገብሯቸው የሚችሉ መፍትሔዎች፦
- አንድ ሰዓት ሙሉ ስፖርት ማሰራት አይጠበቅብዎትም። ጠዋት የ15 ደቂቃ የእግር ጉዞ፣ ከሰዓት የ20 ደቂቃ የሩጫ ጨዋታ፣ ማታ ደግሞ ከቤተሰብ ጋር የ15 ደቂቃ የውዝዋዜ (ዳንስ) ጊዜ በመፍጠር ግቡን በቀላሉ ማሳካት ይቻላል።
- የቤት ውስጥ ስራዎችን ለምሳሌ ክፍል ማስተካከል ወይም እቃዎችን ቦታ ቦታ ማስቀመጥ በሰዓት የተገደበ አስደሳች ውድድር በማድረግ ልጆች እንዲንቀሳቀሱ ማበረታታት።
- በሳምንቱ መጨረሻ ስልኮችን እና ታብሌቶችን ለተወሰነ ሰዓት ዘግቶ በማስቀመጥ፣ ልጆች አማራጭ ፍለጋ ወደ ውጭ ወጥተው እንዲጫወቱና በራሳቸው አዳዲስ ጨዋታዎችን እንዲፈጥሩ መንገድ መክፈት።
- ልጆች የሚሰሙትን ሳይሆን የሚያዩትን ነው የሚከተሉት። በዚህ የሳምንት መጨረሻ ወላጆች ራሳቸው ከልጆቻቸው ጋር በመሆን በእግር መጓዝ ወይም ኳስ መጫወት ሲጀምሩ፣ ልጆቹ እንቅስቃሴን እንደ ግዴታ ሳይሆን እንደ መዝናኛ ማየት ይጀምራሉ።
What's Your Reaction?