የብሪክስ (BRICS) ስብሰባ በኢራን ጉዳይ ምክንያት ያለ የጋራ ስምምነት ተጠናቀቀ!
ሎሚ ዜና ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና የተሰሙ ዋና ዋና ዜናዎች የኢራን ጦርነትና የBRICS መከፋፈል፦ በኒው ዴሊ የተካሄደው የብሪክስ (BRICS) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ፣ በኢራን ጦርነት ዙሪያ አባል ሀገራቱ መግባባት ባለመቻላቸው ያለ የጋራ መግለጫ ተጠናቋል። ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ የሃሳብ ልዩነት አሳይተዋል።
ሎሚ ዜና ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና የተሰሙ ዋና ዋና ዜናዎች
ሩሲያ እና ኢራን አሜሪካንን በግልጽ የሚያወግዝ መግለጫ እንዲወጣ ሲገፋፉ፣ እንደ ህንድ ያሉ ሀገራት ከአሜሪካ ጋር ያላቸውን የንግድና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ላለማበላሸት ሃሳቡን ውድቅ አድርገውታል። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ግብፅ በበኩላቸው የኢራንን የአካባቢው ሀገራት ላይ የምታደርገውን ጥቃት ኮንነዋል።በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ አካባቢ ያለው አለመረጋጋት ለነዳጅ አስመጪዎቹ ቻይና እና ህንድ ትልቅ የኢኮኖሚ ስጋት ቢሆንም፣ ለችግሩ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በፖለቲካዊ ትረካው ላይ መስማማት አልተቻለም።
#ሎሚ_ዜና #ብሪክስ #ኢራን #መካከለኛው_ምስራቅ #BRICS #IranConflict #LomiiNews
What's Your Reaction?