ሜታ 567 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተፈረደበት።

ሜታ 567 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተፈረደበት። በታዳጊዎች የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ላይ ታሪካዊ የፍርድ ቤት ውሳኔ!

Aug 7, 2026 - 12:28
 0  12
ሜታ 567 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተፈረደበት።


ሜታ 567 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተፈረደበት። በታዳጊዎች የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ላይ ታሪካዊ የፍርድ ቤት ውሳኔ!

የፌስቡክ እና ኢንስታግራም እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ በታዳጊዎችና በህፃናት ላይ ለሚያደርሰው የአእምሮ ጤና ጉዳት እና የደህንነት ስጋት 567 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል የኒው ሜክሲኮ ክፍለ ሀገር ዳኛ ብይን አስተላለፉ።

ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በህፃናት ደህንነት ላይ ለሚፈጽሙት ግዴለሽነት ከተላለፉት ትልልቅ የገንዘብ ቅጣቶች እና የህግ ድንጋጌዎች አንዱ ሲሆን፣ ሜታ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ ለታዳጊዎች የአእምሮ ጤና ፈንድ ገቢ እንዲያደርግ ታዟል።

የኒው ሜክሲኮ አቃቤ ህግ ሜታን በፍርድ ቤት የከሰሰው በኢንስታግራም እና ፌስቡክ መድረኮች ላይ ህፃናትን እና ታዳጊዎችን ከአዳኞች (Online Predators)፣ ከፆታዊ ብዝበዛ እና ከአእምሮ ጤና ቀውስ የመጠበቅ ግዴታውን አልተወጣም በሚል ነበር።

በፍርድ ቤቱ የክርክር ሂደት ወቅት የቀረቡት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፦

* አልጎሪዝም:- ሱሰኝነት የሜታ ማህበራዊ ሚዲያ አልጎሪዝሞች ታዳጊዎች በማያ ገጽ (Screen) ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲያረዝሙ እና ለሱሰኝነት እንዲጋለጡ ሆን ተብሎ የተሰሩ ናቸው በሚል ተሞግቷል።

*የአእምሮ ጤና ጉዳት፡- በታዳጊዎች ላይ በተደረጉ ጥናቶች ኢንስታግራም በወጣቶች ላይ ጭንቀት፣ ድብርት እና የሰውነት አካል የማነስ ስሜት (Body Image Issues) እንደሚያስከትል ታውቋል።

* የህፃናት ደህንነት ክፍተት፡- መድረኩ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህፃናት ተስፋፍተው ከሚንቀሳቀሱ ህገ-ወጥ አዳኞች እና አላስፈላጊ ምስሎች ጥበቃ የሚያደርግበት በቂ የደህንነት አሰራር አልነበረውም።

የኒው ሜክሲኮ ክፍለ ሀገር ዳኛ ያስተላለፉት ውሳኔ የገንዘብ ቅጣት ብቻ ሳይሆን ሜታ በመድረኮቹ ላይ መሰረታዊ የአሰራር ለውጦችን እንዲያደርግ ያዛል።

እንደ ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች አስተያየት ከሆነ ይህ ውሳኔ ለሌሎች የቴክኖሎጂ ባላባቶች ማለትም እንደ TikTok፣ Snapchat እና YouTube ያሉ ትልቅ ተቋማት ማስጠንቀቂያ መሆኑን የሳይበር ደህንነት እና የቴክኖሎጂ ህግ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

የሎሜ ቴክኖሎጂ (Lomii Tech) ተንታኞች እንደሚያመለክቱት፣ ይህ ፍርድ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ትርፍን ብቻ ሳይሆን የተጠቃሚዎችን በተለይም የህፃናትን ደህንነት አስቀድመው እንዲሰሩ የሚያስገድድ አዲስ ዓለም አቀፍ ደረጃ (Benchmark) ይፈጥራል። ይህንን ተከትሎ በኢትዮጵያም ህፃናትን ከቴክኖሎጂ ቅኝ ግዛት/ባርነት ለመታደግ የሚያስችል ውሳኔ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል ።

ሜታ በበኩሉ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ለማለት እንደሚቀሳቀስ ቢገልጽም፣ በታዳጊዎች ደህንነት ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚደረጉት የህግ እና የፖሊሲ ጫናዎች ኩባንያው የምርቶቹን አሰራር በጥብቅ እንዲከልስ ያስገድዱታል ተብሎ ይጠበቃል።


ሎሚ ቴክኖሎጂ

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow