ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በደመቀ ድል አጠናቀቁ።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በደመቀ ድል አጠናቀቁ።
በሞሮኮ ራባት በተካሄደው ዓለም አቀፍ የዳይመንድ ሊግ የውድድር መድረክ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደማቅ ድል አስመዝግበዋል።
በተለይም በሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ድንቅ ብቃቷን በማሳየት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቅቃለች። አትሌቷ ርቀቱን ለመጨረስ የፈጀባት ሰዓት 3 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ መሆኑ ተገልጿል።
በዚሁ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ፍልሚያ ላይ ሌላኛዋ ተስፈኛ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሐረገወይን ካልአዩ ፍሬወይኒን በቅርብ ርቀት በመከተል 3 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ ከ28 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ለሀገሯ ድርብ ደስታን አምጥታለች።
በ800 ሜትርም ሌላ ስኬት ተመዝግቧል
በሌላ በኩል በጉጉት በተጠበቀው የሴቶች 800 ሜትር ውድድር ላይ የተሰለፈችው አትሌት ፅጌ ድጉማ ብርቱ ፉክክር አድርጋለች። አትሌት ፅጌ ርቀቱን በ1 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ24 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በ2ኛነት ማጠናቀቅ ችላለች።
በአጠቃላይ በሞሮኮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች ያስመዘገቡት ውጤት በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ያላቸውን የበላይነት በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኗል።
What's Your Reaction?