ኢትዮ ቴሌኮም እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጋርነታቸውን ገመገሙ
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ከአፍሪካ ልማት ባንክ (AfDB) የኮርፖሬት አስተዳደር፣ መሠረተ ልማት እና የግል ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን ኳይኖር እንዲሁም ከባንኩ ከፍተኛ ማኔጅመንት አባላት ጋር ስትራቴጂካዊ ውይይት አካሂደዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ከአፍሪካ ልማት ባንክ (AfDB) የኮርፖሬት አስተዳደር፣ መሠረተ ልማት እና የግል ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን ኳይኖር እንዲሁም ከባንኩ ከፍተኛ ማኔጅመንት አባላት ጋር ስትራቴጂካዊ ውይይት አካሂደዋል።
ይህ ውይይት የኢትዮ ቴሌኮምን የለውጥ ስትራቴጂ ለማስፈጸም እና የሀገሪቱን አጠቃላይ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን እየተደረገ ያለውን የጋራ ጥረት ለመገምገም ያለመ ነው።
በሂደቱም የኢትዮጵያን የዲጂታል እና የቴሌኮም መሠረተ ልማት ለማስፋፋት፣ ለማዘመንና ስትራቴጂካዊ ግቦችን ለማሳካት እየተከናወኑ ያሉ የፋይናንስ ድርድሮች በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
ይህ ትብብር የዲጂታል መድረኮችን በማጠናከር በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች፣ የንግድ ድርጅቶች እና ተቋማት አቅም የሚፈጥሩ አዳዲስና አካታች የዲጂታል አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል
What's Your Reaction?