የቤት ኪራይ መመሪያው የአዲስ ተከራዮችን ሁኔታ ባላካተተ መልኩ በመተግበሩ በዜጎች ላይ ጫና ፈጥሯል
በቅርቡ ስራ ላይ የዋለው የቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ትኩረቱን ነባር ተከራዮች ላይ ብቻ ማድረጉ፣ ለአዲስ ቤት ፈላጊዎች እና ተከራዮች ከፍተኛ የዋጋ ንረትና የማህበራዊ ህይወት ጫና እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ ተገለጸ።
በቅርቡ ስራ ላይ የዋለው የቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ትኩረቱን ነባር ተከራዮች ላይ ብቻ ማድረጉ፣ ለአዲስ ቤት ፈላጊዎች እና ተከራዮች ከፍተኛ የዋጋ ንረትና የማህበራዊ ህይወት ጫና እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ ተገለጸ።
አዋጁ ነባር ተከራዮች ላይ ያነጣጠረ የዋጋ ጭማሪ ገደብ መጣሉን ተንተርሰው፣ አንዳንድ አከራዮች ነባር ተከራዮችን በተለያዩ ምክንያቶች በማስወጣት አዳዲስ ገቢዎችን በተጋነነ ዋጋ ለማከራየት እየሞከሩ እንደሆነ እና ይህም አዲስ ቤት በሚፈልጉና በአሁኑ ወቅት በሚከራዩ ዜጎች ላይ ሊሸከሙት የማይችሉት የኢኮኖሚ ጫና እያስከተለ ይገኛል።
የቁጥጥር ክፍተቱ ያስከተለው ተጽዕኖ በገበያው ላይ እየታየ ያለው አዲስ የሚከራዩ ቤቶች የዋጋ ግዥፈት በብዙ አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ትልቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አደጋ ደቅኗል።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ግለሰቦች እንደሚሉት ከሆነ አከራዮች ከፍተኛ የኪራይ ዋጋ ከአዳዲስ ተከራዮች ለማግኘት ሲሉ፣ ነባር ተከራዮችን ሰበብ እየፈለጉ እንዲወጡ የማድረግ ሁኔታዎች እየተለመዱ መጥተዋል። አዲስ ቤት ፈላጊዎች በገበያው ላይ የሚጠራው ዋጋ ከተጠቃሚው አቅም በላይ በመሆኑ ምክንያት ምቹና ተመጣጣኝ ቤት ለማግኘት ተስፋ ቆርጠናል።" ሲሉ ተደምጠዋል።
አሁን እየታየ ያለው የዋጋ ንረት እንዲቆም እና የቤት ኪራይ ገበያው የተረጋጋ እንዲሆን የሕግ ማዕቀፉ አዲስ የሚከራዩ ቤቶችንም ጭምር ያካተተ ቁጥጥርና መመሪያ ሊያበጅለት ይገባል።
በመሆኑም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የመመሪያውን አፈጻጸም ክፍተቶች በመፈተሽ፣ ለአዲስ ተከራዮች የሚጠራውን የተጋነነ የኪራይ ዋጋ ስርዓት የሚያስይዝ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት አለባቸው።
What's Your Reaction?