የአዲስ አበባ ከተማ ልማት እና የህጻናት መናፈሻዎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለህጻናት መጫወቻ እና ለአረንጓዴ ስፍራዎች የሰጠው ትኩረት በአህጉሪቱ አርአያነቱ እየተመሰገነ ነው የአዲስ አበባ የሕፃናት መጫወቻዎች ልማት ከአፍሪካ ከተሞች አንጻር ሲሻሻለ እና ምሳሊ የሚሆን ነው ተብሎዋል

May 29, 2026 - 19:17
 0  1
የአዲስ አበባ ከተማ ልማት እና የህጻናት መናፈሻዎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለህጻናት መጫወቻ እና ለአረንጓዴ ስፍራዎች የሰጠው ትኩረት በአህጉሪቱ አርአያነቱ እየተመሰገነ ነው የአዲስ አበባ የሕፃናት መጫወቻዎች ልማት ከአፍሪካ ከተሞች አንጻር ሲሻሻለ እና ምሳሊ የሚሆን ነው ተብሎዋል

በአዲስ አበባ በኮሪደር ልማቱ የተገነቡት ዘመናዊ የሕፃናት መናፈሻዎች እንደ አዲሱ 15 ሄክታር ላይ ያረፈው አራዳ ፓርክ እና የሕፃናት ማዕከላዊ ፓርክ ዋና ከተማዋን ለሕፃናት ምቹ ከሆኑ የአፍሪካ መዲናዎች ተርታ እያሰለፏት ይገኛል።

 አዲስ አበባ “Raise a City” በሚል ስትራቴጂ 1.3 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን ተጠቃሚ ያደረገ ፈጣን የመጫወቻ ስፍራዎች ግንባታ በማካሄድ እንደ ናይሮቢ እና አክራ ካሉ ከተሞች የላቀ የመንግስት ቁርጠኝነት እያሳየች  ቢሆንም አሁንም ጋናን ከተማ ኩማሲ ላይ ለመድረስ ግን መስራት እንደሚጠበቅባት ተነግሮዋል

 በከተማዋ የአንድ ሰው የአረንጓዴ ስፍራ ድርሻ 9.7 ካሬ ሜትር የደረሰ ነው የተባለ ሲሆን ይህም ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዝቅተኛ መመዘኛ (9 ካሬ ሜትር) እና እንደ ሩዋንዳዋ ሙሳንዜ (7.5 ካሬ ሜትር) ካሉ ከተሞች ከፍ ያለ ነው። ሆኖም እንደ ጋናዋ ኩማሲ (13.6 ካሬ ሜትር) ካሉ ከተሞች ያንሳል።ለህጻናት መጫወቻ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ለሀገር የወደፊት ምርታማነት የሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው

እንደ ደቡብ አፍሪካዋ ጆሃንስበርግ ዘመናዊ መጫወቻዎችን በየሰፈሩ ለሁሉም ሕፃናት በነጻ ተደራሽ የማድረግ እና የአካል ጉዳተኛ ሕፃናትን ያማከሉ (Inclusive) የማድረግ ስራ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የዘርፉ ባለሙያዎች አሳስበዋል።

 

 

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow