ፊፋ 2026፦ የዓለም ዋንጫ የትኬት ሽያጭ ገበያ እና የስፖንሰርሺፕ ዘመቻዎች

ዓለም ዋንጫው ሊጀመር ከሶስት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ሲቀረው፣ በዚህ ሳምንት እና በሚቀጥለው ሳምንት የዓለም እግር ኳስን እያነጋገሩ ካሉ  ዋና ዋና አጀንዳዎችመካከል የ አለምዋንጫ ስታድየም መግቢያ ትኬት አንዱ ነው 

May 25, 2026 - 13:06
 0  2
ፊፋ 2026፦ የዓለም ዋንጫ የትኬት ሽያጭ ገበያ እና የስፖንሰርሺፕ ዘመቻዎች

2026 የዓለም ዋንጫ የትኬት ሽያጭ ገበያ እና የስፖንሰርሺፕ ዘመቻዎች

የዓለም ዋንጫው ሊጀመር ከሶስት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ሲቀረው፣ በዚህ ሳምንት እና በሚቀጥለው ሳምንት የዓለም እግር ኳስን እያነጋገሩ ካሉ  ዋና ዋና አጀንዳዎችመካከል የ አለምዋንጫ ስታድየም መግቢያ ትኬት አንዱ ነው በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ዝግጅት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት የሳቡ ሁለት ዋና ዋና ክስተቶች ተመዝግበዋል፦

  • የትኬት ገበያው መናወ በይፋዊው የፊፋ የትኬት መድረክ ላይ ያለው ፍላጎት ከሚጠበቀው በላይ በመጨመሩ፣ በጥቁር ገበያ ላይ የሚሸጡ የትኬት ዋጋዎች በከፍተኛ ሁኔታ ንረዋል። ፊፋ ደጋፊዎች በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮች ከሚመዘብሩ የሐሰት ትኬት አጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
  • የስፖንሰርሺፕ ፉክክር፦ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት የዓለም ዋንጫውን ተደራሽነት ለመጠቀም የሚያደርጉት የማስታወቂያ እና የስፖንሰርሺፕ ዘመቻ ከመቼውም ጊዜ በላይ የጦፈ ሲሆን፣ ዲጂታል እና የቪዲዮ ቴክኖሎጂ ተኮር የሆኑ አዳዲስ ስፖንሰሮች ገበያውን እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ።የአለም የኮከብ ተጫዋቾች  የወዳጅነት ጨዋታዎች ከትላንት ጀሮ መካሄድ ጀምረዋል

የዓለም ዋንጫው አስተናጋጅ ሜክሲኮ ከትላት በስቲያ  ምሽት ባደረገችው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ጋናን 2 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች። ጨዋታው አሰልጣኞች ሰኔ 1 ቀን የመጨረሻውን 26 ተጫዋቾች ስብስብ ይፋ ከማድረጋቸው በፊት የተጫዋቾችን ብቃት ለመመዘን ትልቅ ዕድል ፈጥሯል። የፊታችን አርብ ደቡብ አፍሪካ (ባፋና ባፋና) ኒካራጓ ሜክሲኮ አውስትራሊያ (በፓሳዴና፣ ካሊፎርኒያ) እና አሜሪካ ሴኔጋል በሻርሎት፣ ኖርዝ ካሮላይና ስታድየም  የሚደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ  በጉጉት ይጠበቃሉ።

የአርሰናል ታሪካዊ የዘውድ ጭነት እና የፕሪምየር ሊጉ አስገራሚ ማጠቃለያ

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ትላንት እሁድ የተደረጉት ጨዋታዎች በአስደናቂ ድራማዎች ተጠናቀዋል።

  • የመድፈኞቹ ድል፦ ሚኬል አርቴታ የሚመራው አርሰናል ክሪስታል ፓላስን 2 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ፣ 22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን በይፋ አረጋግጧል።
  • የወራጅ ቀጠናው ጭንቅ፦ ቶተንሃም ሆትስፐር ኤቨርተንን 1 0 በማሸነፍ በሊጉ ሲሰነብት፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ሊድስን 3 0 ቢያሸንፍም ሳይረዳው ቀርቶ ወደ ታችኛው ክፍል (ቻምፒዮንሺፕ) መውረዱ ታውቋል።
  • የታላላቆች ስንብት፦ የማንቸስተር ሲቲው ስራ አስኪያጅ ፔፕ ጓርዲዮላ እና የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ኮከብ ሞሃመድ ሳላህ በሊጉ የነበራቸውን ታሪካዊ ቆይታ ትላንት በይፋ አጠናቀዋል።የፕሪምየር  ክለቦች ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ስብስባቸውን የሚያጠናክሩበት የክረምቱ የዝውውር መስኮት በይፋ ይከፈታል። ዘንድሮ የፕሪምየር ሊጉ ውድድር ቀድሞ የተጠናቀቀው ተጫዋቾች በሰኔ እና ሐምሌ ወራት በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ለሚካሄደው ትልቁ የዓለም ዋንጫ በቂ የዝግጅት እና የማገገሚያ ጊዜ እንዲያገኙ ለማድረግ  ሲሆን 2026/27 አዲሱ የፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ዕጣ ማውጫ ሰኔ 12  ከአለም ዋንጫ መክፍቻ ቀን ማግስት ይፋ ይደርጋል ውድድሩ ከዓለም ዋንጫው ማብቂያ በኋላ ነሐሴ 16 ቀን 2018 . ይጀምራል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow