​ሩሲያ አቻ የሌለው የተባለውን ሳርማት ሚሳኤል በስኬት መሞከሯን አስታወቀች

ሩሲያ አቻ የሌለው የተባለውን ሳርማት ሚሳኤል በስኬት መሞከሯን አስታወቀች ሩሲያ በዓለም ላይ እጅግ ኃይለኛ የተባለውንና የኒውክሌር አቅም የታጠቀውን አዲሱን ሳርማት (Sarmat) አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ መሞከሯን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይፋ አደረጉ።

May 13, 2026 - 21:01
 0  1
​ሩሲያ አቻ የሌለው የተባለውን ሳርማት ሚሳኤል በስኬት መሞከሯን አስታወቀች

ሩሲያ በዓለም ላይ እጅግ ኃይለኛ የተባለውንና የኒውክሌር አቅም የታጠቀውን አዲሱን ሳርማት (Sarmat) አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ መሞከሯን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይፋ አደረጉ።

በምዕራባውያን ዘንድ "ሰይጣን ሁለት" (Satan II) ተብሎ የሚጠራው ይህ ዘመናዊ መሣሪያ፣ ከ35,000 ኪሎ ሜትር በላይ የመጓዝ ብቃቱና አሁን ካሉ እንዲሁም ወደፊት ከሚመጡ የፀረ-ሚሳኤል መከላከያ ሥርዓቶች ውስጥ ሰርጎ የመግባት ችሎታው ልዩ እንደሚያደርገው ተገልጿል።

የሩስያ የስትራቴጂክ ሚሳኤል ጦር አዛዥ ሰርጌይ ካራካዬቭ ለፕሬዝዳንቱ ባቀረቡት ሪፖርት መሠረት፣ ሙከራው በታቀደለት መልኩ መከናወኑ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ፑቲንም መሣሪያው እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ወደ ፍልሚያ አገልግሎት እንደሚገባ አረጋግጠዋል።

​ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ከ2011 ጀምሮ ሲለማ የቆየና የድሮውን የሶቪየት ዘመን ቮዬቮዳ ሚሳኤሎችን ለመተካት ታስቦ የተሰራ ሲሆን፣ ካለፉት ዓመታት የሙከራ ውድቀቶችና በ2024 ከደረሰበት ከፍተኛ ፍንዳታ በኋላ የተመዘገበ ትልቅ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል። ሳርማት ከምዕራባውያን አቻዎቹ በአራት እጥፍ የሚበልጥ የጦርነት አቅም እንዳለው የተነገረለት ሲሆን፣ ፕሬዝዳንት ፑቲን መሣሪያው የሩሲያን ደህንነት ለማስጠበቅና በሀገሪቱ ላይ ጥቃት ለማድረስ ለሚያስቡ ወገኖች ማስጠንቀቂያ እንደሚሆን ገልጸዋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow