የውጭ ኃይሎች የሱዳንና ኢትዮጵያን ግንኙነት ለማሻከር የሚያደርጉት ጥረትና የራሻ አዋድ እይታ

​ሰሞኑን በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተስተዋለው ውጥረት የሱዳናውያንን ፍላጎት የማይወክልና በውጭ ኃይሎች፣ በተለይም በግብፅ አቀነባባሪነት የሚመራ አጀንዳ መሆኑን ሱዳናዊቷ ጋዜጠኛ ራሻ አዋድ ገለጸች። 

May 19, 2026 - 10:41
 0  2
የውጭ ኃይሎች የሱዳንና ኢትዮጵያን ግንኙነት ለማሻከር የሚያደርጉት ጥረትና የራሻ አዋድ እይታ

​ሰሞኑን በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተስተዋለው ውጥረት የሱዳናውያንን ፍላጎት የማይወክልና በውጭ ኃይሎች፣ በተለይም በግብፅ አቀነባባሪነት የሚመራ አጀንዳ መሆኑን ሱዳናዊቷ ጋዜጠኛ ራሻ አዋድ ገለጸች። 

ጋዜጠኛዋ በቅርቡ ከሱዳን ጦር ኃይሎች በኩል በኢትዮጵያ ላይ የተሰነዘረው ክስ መሰረተ ቢስ መሆኑን በመጥቀስ፣ ሙከራው ግብፅ ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ጋር ለማጋጨት የምታደርገው ሴራ አካል ነው ብላለች።

 በልማትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተውን የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ትስስር የሚጎዳው ይህ ዘመቻ ከሱዳን ብሔራዊ ጥቅም ጋር እንደማይገናኝ ያብራራችው ራሻ፣ ሱዳን በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሁልጊዜ የግብፅን አቋም ከማስተጋባት ወጥታ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስቀድም ገለልተኛ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መገንባትና ራሷን ከግብፅ ጣልቃ ገብነት ማራቅ እንዳለባት አሳስባለች። 

አክላም አንዳንድ የሱዳን ጦር መሪዎች ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሲሉ የውስጥ ቀውሱን ወደ ውጭ ለመግፋት እየሞከሩ መሆኑን በመጠቆም፣ ወደ ቀጣናዊ ውጥረት እያመራ ያለውን የሱዳን ጦርነት ለማስቆም መፍትሄው ከውስጥ መጀመር እንዳለበትና ከኃይል አማራጭ ይልቅ ለውይይትና ለዲፕሎማሲ ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስባለች።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow